አለም ወደ አንድ መንደርነት በተቀየረችበት በዚህ ዘመን በኤሌክትሮኒክ የግብይት ስራ (ኢ,-ማርኬቲንግ) የሚካሄድ የንግድ ልውውጥ ዘመኑን የዋጀ የንግዱ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት ሆኗል፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ጊዜ ድርጅቶች ምርታቸውን እና/ወይም አገልግሎታቸውን ለተጠቃሚው የሚያደርሱበት መንገድ ስር ነቀል በሆነ ሁኔታ ተቀይሯል፡፡ ደንበኞች ማንኛውንም የሚገዙትን እቃ ወይም አገልግሎት ባሉበት ቦታ በቤታቸው በማንኛውም ጊዜ ሆነው በኦንላይን ግዢ መፈጸም እና አስደናቂ የሆነ ግብይት ለማድረግ ይችላሉ፡፡

በአሁኑ ጊዜ ኢ-ግብይት ተፈላጊነቱ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት እያንዳንዱ በንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ድርጅት መሸጥ ወይም መግዛት የሚፈልገውን ምርት እና አገልግሎት በኦንላይን ስቶር ግዢ አማካኝነት በጣም ብዙ ለሆኑ ደንበኞች ለሽያጭ ማቅረብ እና መሸጥ ወይም መግዛት ይችላል፡፡

በመሆኑም አቅራቢ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የተባለው ድርጅታችን ለተጠቃሚዎች አመቺ የሆነ የኦንላይን የግብይት ቦታ በማዘጋጀት ማንኛውም ድርጅት ወይም ግለሰብ የፈለገውን ዕቃ ወይም አገልግሎት መግዛትም ሆነ መሸጥ ይችል ዘንድ ሲያቀርብልዎ ላቅ ያለ ደስታ ይሰማዋል፤ ኑ አብረን እንስራ በማለትም በአክብሮት ይጋብዛችኋል፡፡

Share to friends
Shopping cart
There are no products in the cart!
Continue shopping
0